የውጭ ኦዲተሮች ማኅበር የሪፖርት አቀራረብና የደንበኛ ተግባቦት ክህሎት ሥልጠና ከኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር ለአባላት እና በስራቸው ተቀጥረው ለሚሰሩ ኦዲት ኃላፊዎች ሰጥቷል።
የውጭ ኦዲተሮች ማኅበር ከኢትዮጵያ እንግሊዝኛ ቋንቋ ባለሙያዎች ማኅበር ጋር በመተባበር በሪፖርት አቀራረብና የደንበኛ ተግባቦት ክህሎት ላይ የአንድ ቀን ስልጠና ፕሮግራም ለአባላቶቹ እና በስራቸው ተቀጥረው ለሚሰሩ የኦዲት ኃላፊዎች (ሰኔ 13/ 2016 በቤስት ዌስተርን ፕላስ ፒሪያል አዲስ ሆቴል) አዘጋጅቷል። ይህ በክህሎት ላይ የተመሰረተ እና የተግባር ስልጠና ተሳታፊዎችን ከደንበኞቻቸው ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት ውጤታማ ለማድረግ አስፈላጊ የሆኑትን ክህሎቶች እና ልምዶችን ለማዳበር እንዲረዳ ታስቦ ተዘጋጀ የማነቃቂያ ስልጠና ሲሆን ኦዲተሮች ሪፖርታቸውን በተገቢው መንገድ ለተጠቃሚዎች ለማቅረብ እና ደንበኛቸው በቀረበው ሪፖርት ላይ በቂ ግንዛቤ አግኝቶ በሚወስነው ውሳኔ ላይ እምነት እንዲኖረው የባለሞያው ገለጻ ጠቃሚ በመሆኑ ይህን ለማሳካት ያለመ ነው።
ሰኔ 13፣ 2016፣ አዲስ አበባ፡-
Share This News